የጅቡቲ የጸጥታ ኅይሎች “አሸባሪዎች” ብለው በገለጹት አማጺ ቡድን ላይ በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ባደረጉት የድሮን ድብደባ ስምንት የቡድኑ አባላትን እና ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪሎችን መግደላቸውን ባለሥልጣናቱ ትላንት ዕሁድ አስታውቀዋል።
አዶራታ በተባለና ከኢትዮጵያ ድንበር ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ የድሮን ጥቃቱ እንደተፈጸመ የጅቡቲ የመከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ አመልክቷል።
“ስምንት አሸባሪዎች ተገድለዋል” ያለው መግለጫ፣ “ነገር ግን የሃገሪቱ ሲቪል ዜጎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል” ብሏል።
ቡድኑ በጅቡቲ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ስጋት የሚደቅኑ አድራጎቶች ውስጥ መግባቱ እንደታወቀና ምርመራም እንደተደረገ የመከላከያ ሚኒስቴሩ መግለጫ ጨምሮ አመልክቷል።
ጥቃቱ የተፈጸመው በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ እንደሆነ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን ሪፖርት ጅቡቲ አስተባብላለች፡፡
የአፍሪካ ቀንድ የሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት ከጅቡቲ የፀጥታ ኃይሎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ላቀረበው ጥያቄ መልስ ሳያገኝ ቀርቷል።
መድረክ / ፎረም