ፍልስጤማውያን በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ካን ዩኒስ ላይ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ድብደባ የተገደሉ ዘመዶቻቸውን ቤተሰቦች ዛሬ ሐሙስ ሲያስተዛዝኑ ውለዋል፡፡
የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ እንዳስታቀው በአል-አማል ሆስፒታል አቅራቢያ በተደረገ አንድ የአየር ጥቃት በትንሹ 10 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 12 ሰዎች ቆስለዋል።
አብዛኛው የከተማዋ ህዝብ ለቆ ቢወጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች በአል-አማል አቅራቢያ እና ሌላኛው ሆስፒታል አካባቢ ተጠልለው እንደነበር አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ነዋሪዎቹ በሕክምና ተቋማቱ አቅራቢያ የሰፈሩት ከቦምብ ጥቃቱ እንደሚድኑ ተስፋ በማድረግ እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል፡፡
ጦርነቱ እስካሁን ከ20,000 በላይ ፍልስጤማውያንን የገደለ ሲሆን 2.3 ሚሊዮን ከሚደርሰው የጋዛ ህዝብ 85 በመቶ የሚሆነውን ከመኖሪያ ቤታቸው አፈናቅሏል።
አብዛኛው ሰሜናዊ ጋዛ አካባቢ የተደመሰሰ ሲሆን በአብዛኛው ህዝብ ከቀሪው ግዛት ለሳምንታት ተነጥሎ መቆየቱን ዘገባው ጠቅሷል፡፡
እስራኤል ጥቃቷን ወደ አብዛኞቹ ትናንሽ አካባቢዎች ሳያቀር ያሰፋች ሲሆን ብዙዎች የደቡብ አካባቢዎች ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል የሚል ስጋት መፍጠሩ ተመልክቷል፡፡
መድረክ / ፎረም