አዲስ አበባ —
ለሥድስት ወራት የቤት ክራይ ለመክፈል ቃል የገባልን የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና የአካባቢው አስተዳደር ከሁለት ወራት በኋላ ሜዳ ላይ በትኖናል ሲሉ የሶማሌ ክልል ተፈናቃዮች በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች ን አማረሩ፡፡
ተቃዋሚው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ለእነዚህ ወጣቶች ለሌሎችም ተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ ከፍ እንዲል ጠይቋል፡፡ በወጣቶቹ የቀረበው ቅሬታ ተገቢ መሆኑን የገለፀው የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ ተጨማሪ ሁለት ወራት የቤት ኪራይ እንዲከፈልላቸው መወሰኑን አስታውቋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ