ድሬዳዋ —
“ከዕሁድ አንስቶ ጥቃት እየተፈፀመብን ስለሆነ ዩኒቨርሲቲው መፍትኄ ይስጠን ወይም ወደየቤተሰቦቻችን ይመልሰን” ብለዋል ተማሪዎቹ።
የድሬዳዋ የሐይማኖት ተቋማት ጉባዔ ሰብሳቢ ሊቀብርሃናት ቀለመወርቅ ከተማሪዎቹና ከአስተዳደሩ ጋር በመወያየት አንዳንድ የመፍትሔ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ማግባባታቸውን ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ ከብዙኃኑ ተማሪ ጋር በመወያየት ጊዜ የሚፈልጉ ችግሮችን በሂደት እንደሚፈታ ገልፆ ከተማሪዎች ጋር ትምህርት እንዲጀምሩ ተስማምተናል ብሏል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ