ድሬዳዋ —
የድሬዳዋ አስተዳደር የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የቅዳሜና እሁድ የመንገድ ላይ ገበያ መጀመሩን አስታወቀ። ከዚራ የቀድሞ ማዘጋጃ ቤት የተጀመረው የቅዳሜና እሁድ ገበያ በቀጣይ ወደሌሎች አራት ሰፈሮችም እንደሚስፋፋ አስተዳደሩ አስታውቋል።
ሸማቾችም በመደበኛው ገበያ ከሚያገኙት ባነሰ ዋጋ ልዩ ልዩ ምርቶችን እየገዛን ነው ብለዋል። ገበያው ጊዜያዊ ገበያን ለማረጋጋት ብቻ ሳይሆን ዘላቂነት እንደሚኖረው ነው የተነገረው።