No media source currently available
የፌዴራል መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ ለሦስት ወር ገደማ ያሰለጠናቸውን የመቶና የጓድ አመራሮችን እንዲሁም የማዕረግ ተሿሚ የበታች ሹም አመራሮችን አስመርቋል። ሥልጠናው የፀረ ሽብር እንቅስቃሴውን ከመደገፍ ባሻገር በያዝነው ዓመት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ያግዛል ተብሏል።