በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የድሬዳዋ ፓርቲዎች ምርጫው “ሰላማዊና ፍትኃዊ ነበር” አሉ


የድሬዳዋ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት - ድሬዳዋ
የድሬዳዋ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት - ድሬዳዋ

የድሬዳዋ አስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በድሬዳዋ የተካሄደውን ምርጫ ሰላማዊ ነበር ብሏል። ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎችም የህዝቡን ውሳኔ እናከብራለን ብለዋል። በዚሁ መድረክ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር አመራሮች በቀጣይም በድሬዳዋ ልማት ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በ6ኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ድሬዳዋ ላይ ተሳታፊ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በድሬዳዋ የተካሄደው ምርጫ ሰላማዊ ነበር ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት ሰብሳቢ የኢዜማው አቶ ዮናስ በልሁ 9ኙን ፓርቲዎች ወክለው ባቀረቡት የአቋም መግለጫ ከምርጫው ሰላማዊነት ባሻገር የጸጥታ ሃይሎችና አስተዳደሩ ለምርጫው ስኬት ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋናውን አቅርቧል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የድሬዳዋ ፓርቲዎች ምርጫው “ሰላማዊና ፍትኃዊ ነበር” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:39 0:00


XS
SM
MD
LG