በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድሬዳዋን የሚያስተዳድሩ ፓርቲዎች በብልጽግና ሥር በጋራ ለመስራት ተስማሙ


ከህወሓት በስተቀር ድሬዳዋን በጣምራ የሚያስተዳድሯት ሦስቱ የቀድሞ የኢህአዴግ ድርጅቶች ፣ እንዲሁም አጋሮቹ ሶዴፓና ሐብሊ በብልጽግና ፓርቲ ሥር በጋራ ሊሰሩ ተፈራርመዋል።

ህወሓት እስካሁን የብልፅግና ፓርቲን እንዳልተቀላቀለ ይታወቃል። የፓርቲዎቹ አመራሮች በብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራምና ደንብ ዙሪያ ለሁለት ቀናት ውይይት ያካሄዱ ሲሆን ተጨማሪ ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል በተባሉ ጉዳዮች ላይ ሌላ መድረክ ተዘጋጅቶ ዶ/ር አለሙ ስሜ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዶ/ር አለሙ ስሜ ህወሓት በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራምና ደንብ ላይ ከተወያዩ በኋላ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ሊቀጥሉ ወይም ላይቀጥሉ እንደሚችሉ ገልፀው መቀጠል ካልፈለጉ ግን የብልፅግና ፓርቲን ሃሳብ በሚደግፉ የትግራይ ተወላጆች ፓርቲው ትግራይ ውስጥ ቅርንጫፍ እንደሚኖረው አስታውቀዋል። አቶ ለማ መገርሳም የሃሳብ ልዩነታቸውን ሚዲያ ላይ ከማቅረባቸው በፊት ለፓርቲው ቢያቀርቡ የተሻለ ነበር ብለዋል ዶ/ር አለሙ።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ድሬዳዋን የሚያስተዳድሩ ፓርቲዎች በብልጽግና ሥር በጋራ ለመስራት ተስማሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:37 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG