በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሌ ክልል ከፍተኛ የመብት ጥሰት ተፈጽሟል- የድሬደዋ ከተማ የቀድሞ ፖሊስ አባልና ኃላፊ


ድሬዳዋ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ

ግለሰቡ ቀድሞውኑ በሥነ ምግባር ችግርና በሥራ አፈፃፀም ተገምግመው ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው በኋላ ከሥራ የተባረሩ ናቸው-የድሬዳዋ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤትና የካቤኔ ጉዳዮች ኃላፊ።

የኢሕአዴግ መንግሥት ሥልጣን ከያዘ ወዲህ በሶማሌ ክልል በሕዝብ ላይ ያልተቋረጠ የመብት ጥሰት ይካሄዳል ያሉ የቀድሞ የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ዋና ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሻለቃ ዓሊ ሲምሬ ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ባለፈው ታኅሣስ ዐስራ አምስት ዝግጅታችን ማቅረባችን ይታወሳል፡፡

በስደት ከሃገር ውጭ የሚገኙት ዓሊ ሲምሬ ሰገድ ትውልድና ዕድገታቸው ድሬዳዋ ሽንሌ ዞን እንደሆነና እ.ኤ.አ ከ2001 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባል እንደነበሩ ገልፀውልናል፡፡

በወንጀል ምርመራ ኃላፊነትና በልዩ ልዩ ሹመት ሲያገለግሉ ቆይተው በድሬዳዋ ባለሥልጣናት በሙስና ተወንጅለው አንድ ዓመት ከታሠሩ በኋላ የድሬዳዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነፃ እንዳሰናበታቸው በቃለ ምልልሱ ወቅት ገልፀውልናል፡፡

ሻለቃ ዓሊ ሲምሬ የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር ደጋፊዎች ናችሁ በሚል ፤ የሶማሌ ክልል ሕዝብን በጅምላ በመግደል፣ ሴቶችን በመድፈር እና ንብረት የማውደም ወንጀል በኢሕዴግ እንደተፈፀመበት ይናገራሉ ፡፡

ቃለ ምልልሱን የተከታተሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ከፍተኛ አመራር እና የድሬዳዋ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤትና የካቤኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሀሰን ጣሂር በሻለቃ ዓሊ ሲምሬ የተዘረዘሩ ወንጀሎችን አስተባብለዋል፡፡

በተጨማሪም ዓሊ ሲምሬ በሥነ ምግባር ችግርና በሥራ አፈፃፀም ተገምግመው ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው በኋላ ከሥራ የተባረሩ ናቸው፡፡ ስለ ሶማሌ ክልል የሚያውቁት ነገር የለም ብለዋል፡፡

ትዝታ በላቸው የሁለቱን ወገኖች የርስ በርስ ክስ አጠናቅራ ቀጣዩን አዘጋጅታለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በሶማሌ ክልል ከፍተኛ የመብት ጥሰት ተፈጽሟል- የድሬደዋ ከተማ የቀድሞ ፖሊስ አባልና ኃላፊ
please wait

No media source currently available

0:00 0:23:19 0:00

XS
SM
MD
LG