በድሬዳዋ አስተዳደር የአመት በዓል ገበያ የእርድ እንስሳት ላይ እና የባህል አልባሳት ላይ ቅናሽ ሲታይ ሽንኩርትና ቲማቲምን የመሰሉ የአትክልት ውጤቶች ላይ ግን ከበዓሉ በፊት ጀምሮ የተከሰተው የዋጋ መናር አሁንም እንደቀተለ መሆኑን ሸማቾችና ሻጮች ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።
ወሩ የትምህርት መጀመሪያ በመሆኑና ወላጆች ለልጆቻቸው አልባሳት፣ ደብተርና መመዝገቢያ ወጪ ስላለባቸው እንዲሁም በኑሮ ውድነቱ ምክንያት የአመት በዓል ገበያው በጠበቁት ልክ አለመሆኑን ሻጮች ገልጸዋል።
መድረክ / ፎረም