በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ውስጥ “ባለፈው ሳምንት 26 ሰዎች በመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች ተገደሉ” ሲሉ የዐይን እማኞች ለቪኦኤ ተናግረዋል።
"የጉምዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ" በሚባሉ ታጣቂዎች ላይ መንግሥት ህግ የማስከበር እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የገለፁት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር የመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች የተባለውን ግድያ አለመፈፀማቸውን በመጥቀስ አስተባብለዋል።
በዚህ ዙሪያ የድባጤ ወረዳ አስተዳዳሪ “ጉዳዩ ይመለከተዋል” ወዳሉት የማዘዣ ማዕከል አስተባባሪ እንደመሩትና ወደ አስተባባሪው በተደጋጋሚ ያደረገው የስልክ ጥሪ እንዳለተመለሰለት የጠቆመው ሪፖርተራችን ነው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።