በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሚየል ዲያስ-ካኔል ቀጣዩ የኩባ ፕሬዚዳንት ሆነዋል


ሚየል ዲያስ-ካኔል
ሚየል ዲያስ-ካኔል

ሃምሳ ሰባት ዓመት ዕድሜአቸው ላይ የሚገኙት ዲያዝ ካነል በፕሬዚዳንትነት የተሰየሙት ለመጭዎቹ አምስት ዓመታት የሥልጣን ዘመን ሲሆን ከካስትሮ ቤተሰብ ውጭ የሆነ ሰው ኩባን ሲመራ በስድሣ ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው ሰው መሆናቸው ነው።

ሃምሳ ሰባት ዓመት ዕድሜአቸው ላይ የሚገኙት ዲያዝ ካነል በፕሬዚዳንትነት የተሰየሙት ለመጭዎቹ አምስት ዓመታት የሥልጣን ዘመን ሲሆን ከካስትሮ ቤተሰብ ውጭ የሆነ ሰው ኩባን ሲመራ በስድሣ ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው ሰው መሆናቸው ነው።

አዲሱ ፕሬዚዳንት ዛሬ ቃለመሃላ ሲፈፅሙ የካስትሮን አብዮት እንደሚቀጥሉ ቃል የገቡ ሲሆን ቀድሞም ቢሆን የተለየ ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ አለመጠበቁ ተነግሯል።

የ86 ዓመቱ ራውል ካስትሮ ከአሥር ዓመታት በኋላ ሥልጣናቸውን ያስረከቡ ሲሆን የኩባን አብዮት መርተው በ1951 ዓ.ም. /በኢት. የዘ. አ./ ሥልጣን የተቆናጠጡት ታላቅ ወንድማቸው ፊደል ካስትሮ በ2000 ዓ.ም. በጤና መታወክ ምክንያት እስከወጡ ድረስ ሃገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነትና በፕሬዚዳንትነት ግማሽ ምዕት ዓመት ለሚሆን ጊዜ መርተዋል።

በአዲሱ አመራር ወጣቶች ከፍ ወዳሉ የአመራር እርከኖች ቢዘልቁም ራውል ካስትሮና ለሎችም አንጋፋ የሚባሉ የአብዮቱ ሰዎች የኮምዩኒስት ፓርቲውን አመራር ተቆናጥጠው የሚቆዩ በመሆኑ በመሠረቱ ሥልጣኑ በካስትሮና በአጋሮቻቸው እጅ ውስጥ እንደሚቆይ ተነግሯል።

የሃገሪቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉት ሚየል ዲያስ-ካኔል የማኅበራዊ ነፃነት አስተሳሰብ አራማጅ ሲሆኑ ያረጀውን የኮምዩኒስት ፓርቲ አመራር ለመረከብ ብዙ ናቸው የሚል ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ሰው እንደሆኑ ይነገራል።

አዲሶቹ መሪዎች እጅግ የተዳከመውን ምጣኔ ሃብት እንዲያንሠራራ የሚያደርጉ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት በተለይ በትረምፕ አስተዳደር ዘመን ምን ሊሆን እንደሚችል ግልፅ አይደለም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG