ዋሺንግተን ዲሲ —
“ኢትዮጵያን አድን ግብረኃይል” በተባለ ኢትዮጵያውያን ስብስብ የተጠራ የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ በዋሺንግተን ዲሲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊት ለፊት ተካሂዷል፡፡ የሰልፉ አስተባባሪዎች እንደተናገሩት ዓላማው “ሃገራችን አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለውጭም ዓለም ሆነ ለኢትዮጵያውያንም ማኅበረሰብ ለማሳወቅና ኢትዮጵያን ለማጥፋት ተቀናጅተው የሚሰሩ ጽንፈኞችን ለመቃወም ነው” ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የሰልፉ አስተባባሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት “ዓላማችን መንግሥትን መቃወም ሳይሆን በሀስት ክስ የታሰሩ እንደ እስክንድር ነጋ ያሉ የባልደራስ አመራሮች ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትና ሌሎችም የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ለማሳሰብ ነው” ብለዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።