በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ የረጅም ዘመን ሴት እንደራሴዋ ዳያን ፋይንስታይን በሞት ተለዩ


የዲሞክራቲክ ፓርቲን በመወከል የካሊፎርኒያ እንደራሴ የነበሩት ዳያን ፋይንስታይን
የዲሞክራቲክ ፓርቲን በመወከል የካሊፎርኒያ እንደራሴ የነበሩት ዳያን ፋይንስታይን

በድጋሚ የታደሰ

የዲሞክራቲክ ፓርቲውን በመወከል የካሊፎርኒያ እንደራሴ የነበሩት ዳያን ፋይንስታይን፣ በ90 ዓመት ዕድሜአቸው፣ ዛሬ ዐርብ፣ ከዚኽ ዓለም በሞት እንደተለዩ ታውቋል።

በአሜሪካ ከሴቶች የረጅም ዘመን እንደራሴዋ፣ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እንዳረፉ ቢሯቸው አስታውቋል።

“የሴቶች ዓመት” ተብሎ በተጠራው እ.አ.አ ከ1992 ጀምሮ ላለፉት 30 ዓመታት እንደራሴ የነበሩት ዳያን ፋይንስታይን፣ በአካባቢም ኾነ በብሔራዊ ደረጃ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ሚና ተጫውተዋል፤ ተብሏል።

“ፈር ቀዳጅ” ሲሉ እንደራሴዋን የገለጹት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የእርሳቸውም ኾነ የባለቤታቸው ጂል ባይደን ውድ ጓደኛ እንደነበሩ ተናግረዋል።

ለዘብተኛ አቋም እንዳላቸው የሚነገርላቸው እንደራሴዋ፥ የአካባቢ ጥበቃ፣ የሴቶች መብት፣ የመሣሪያ ቁጥጥር በመሰሉ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አቀንቃኝ እንደነበሩ ተዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG