በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አረፉ


ሊቀ ጳጳስ አቡነ እጦንኒዮስ
ሊቀ ጳጳስ አቡነ እጦንኒዮስ

በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሪ ሊቀ ጳጳስ አቡነ እጦንኒዮስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ የካቲት 3/2014 ዓ/ም ሰአፋ በሚገኘው ሰፋአ በሚገኘው የትውልድ መንደራቸው እንድርያስ ገዳም ከጠዋቱ 3 ተፈፀመ። ሊቀ ጳጳስ አቡነ እጦንኒዮስ ከዐስር ዓመታት በላይ በኤርትራ በቁም እስር አሳልፈዋል።

በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ መሰብሰቡን፣ ብዙዎቹም ረጅም ርቀት በእግር ተጉዘው የመጡ መሆናቸውን የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል።

መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይግባ በሚለው ጠንካራ አቋማቸው እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በመጠየቃቸው እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2006 ዓ/ም አንስቶ ከቤተክርስቲያኒቱ መሪነታቸው እንዲነሱ መደረጋቸውና እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2017 ዓ/ም ለአጭር ጊዜ ከተፈቀደላቸው እና ወዲያው ከተቋረጠው በስተቀር እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በቁም እስር እንዲቆዩ መደረጋቸው ይታወቃል።

በዚህም የዜጎችን መብት በመጣስ የሚወነጀለው የኤርትራ መንግሥት ከመብት ድርጅቶች፣ ከአውሮጳ ፓርላማ፣ ከፈረንሳይ እና ከዩናይትድ ስቴትስ መንግሥታት ትችት ቀርቦበታል።

አቡነ እንጦንዮስ የነበሩበትን ሁኔታ በህሊና እስረኝነት የምትመለከተው ዩናይትድ ስቴትስ እስራቸው የሃይማኖት ነጻነትን የተጋፋ ነው ብላ ታምናለች።

አስመራ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ባወጣው የሃዘን መግለጫ መልዕክቱ ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ የቁም እስር ላይ በቆዩት የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንጦንዮስ ማለፍ ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶናል ብሏል።

የለንደኑ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አንባ አንጋዕሎ አቡኑ በጸሎት እንዲታሰቡ ጠይቀዋል። ዓለም አቀፍ የክርስቲያን ሕብረት የተባለው መንፈሳዊ ድርጅት (CSW) መስራች ፕሬዚዳንት ሜርቪን ቶማስ በበኩላቸው ሟቹን ፓትርያርክ "ጥልቅ መርህ የነበራቸው ሰው ነበሩ" ብለዋቸዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ የዓለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን እንደገዘገበው ሐምሌ 12/1927 ዓ/ም የተወለዱት አቡነ እንጦንዮስ በአምስት ዓመት ዕድሜያቸው ነበር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ወደ ገዳም የተላኩት።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2004 ዓ/ም ነበር ሦስተኛው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የተሾሙት።

XS
SM
MD
LG