በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሃት ከ100 በላይ የኮምቦልቻ ወጣቶችን መግደሉን መንግሥት አስታወቀ


ደሴ
ደሴ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በውጊያው የውጭ ኃይሎች ተሳትፈዋል ብለዋል

በወሎ ግንባር በነበረው ውጊያ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከህወሃት ሃይሎች ጋር መሳተፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይሄንን ያስታወቁት ለከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ማብራሪያ ነዉ።

በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ እና የኢትዮጵያውያ ዝርያ የሌላቸው ሰዎች ተሰልፈው መስዋትነት መክፈላቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የተጠቀሱት ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎች የትኛቹ አገራት ዜጐች እንደሆኑ ግንጠቅላይ ሚኒስትሩ አልገለፁም።

በሌላ ዜና ደሴና ኮምቦልቻ ሰርገው የገቡት የህወሃት ኃይሎች “ከ100 በላይ ወጣቶችን ገድለዋል” ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ታጣቂዎቹ ንብረቶችን እያወደሙና እየዘረፉም ነው ሲሉ ከሰዋል።

የህወሃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ትናንት እሁድ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል፤ ህወሃት በጦርነቱ የበላይነት በመያዝ ደሴ ከተማን ተቆጣጥሯል ብለው ነበር።

የትግራይ ክልል ወታደራዊ ማዘዣ መሆኑን የተናገረ አንድ ክፍልም ባወጣው መግለጫ፤ ባለፈው ቅዳሜ ደሴን ትናንት እሁድ ደግሞ ኮምቦልቻን ይዣለሁ ብሏል።

በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፤ ህወሃት ደሴን እና ኮምቦልቻን የመቆጣጠሩ ዜና ዩናይትድ ስቴትስን ስጋት ውስጥ እንደከተታት ገልፀው፤ “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ እንዲያቆሙ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ትላንት የተሰበሰበው የአማራ ክልል ምክር ቤት ማንኛውም የመንግሥት ተቋማት መደበኛ አገልግሎታቸውን እንዲያቋርጡ፤ በጀትና ተሸከርካሪዎቻቸውንም “የህልውና ትግል” ሲል ለሰየመው ዘመቻ እንዲውል መወሰኑን አስታውቋል።

በሌላ ዜና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በበኩላቸው “ህወሃትን ለመመከት” ሕዝቡ እንዲነሳ ጥሪ አቅርበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ህወሃት ከ100 በላይ የኮምቦልቻ ወጣቶችን መግደሉን መንግሥት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:50 0:00


XS
SM
MD
LG