በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደሴና የአካባቢው ዜና


ደሴ ከተማ
ደሴ ከተማ

ደሴና አካባቢዋ “በፌደራል መከላከያ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ነች” ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ፅህፈት ቤት ዛሬ አስታውቋል።

ቀደም ሲል ግን ኃይሎቻቸው ከተማዪቱን ዛሬ መያዛቸውን የህወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ መናገራቸውን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

አቶ ጌታቸው “የትግራይ ኃይሎች የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይሎችን ከደሴ አስወጥተው ወደ ኮምቦልቻ አቅጣጫ እያመሩ ናቸው” ማለታቸውን ሮይተርስ ቢጠቅስም የመንግሥቱ መግለጫ ግን “ሌሊቱን ሙሉ ከተለያዩ ግንባሮች ጠጋግኖ በማሰባሰብ፣ ደሴን ለመያዝ በኩታበር፣ ቦሩ ስላሴና፣ በሃይቅ መስመር የመጣውን ወራሪ መንጋ የፀጥታ ሃይላችን በታላቅ ጀብዱ መክቶታል” ብሏል።

ሮይተርስ የአቶ ጌታቸው ረዳንና የከተማዋ ነዋሪዎች ናቸው ያላቸውን የዓይን እማኞች ጠቅሶ ታጣቂዎቹ ዛሬ ከተማዋን መቆጣጠራቸውን ዘግቧል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ “አንዳንድ የውጪ መገናኛ ብዙሃንም የሽብር ቡድኑን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እያስተጋቡ ይገኛሉ” ሲል ወቅሷል።

የአሜሪካ ድምፅ መረጃውን ከከተማው ነዋሪዎች ለማጣራት ያደረገው ጥረት በከተማይቱ የስልክ አገልግሎት በመቋረጡ ሳይሳካለት ቀርቷል።

XS
SM
MD
LG