በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦሪያዊያን ቤተሰቦቻቸውን በአሰቃቂው ወህኒ ቤት በከፍተኛ ጭንቀት ሲፈልጉ ውለዋል


ሦሪያዊያን ከአሰቃቂው እና ከመሬት በታች በሆነው ወህኒ ቤት ቤተሰቦቻቸውን እየፈለጉ፣ በሴድናያ እስር ቤት፣ እአአ ታኅሳስ 9/2024
ሦሪያዊያን ከአሰቃቂው እና ከመሬት በታች በሆነው ወህኒ ቤት ቤተሰቦቻቸውን እየፈለጉ፣ በሴድናያ እስር ቤት፣ እአአ ታኅሳስ 9/2024

በዘግናኝነቱ የታወቀውን ወህኒ ቤት አማጺያኑ መክፈታቸውን ተከትሎ ትላንት ደብዛቸው የጠፋባቸውን የቤተሰብ አባላት ፍለጋ ሲያስሱ የዋሉ ሦሪያዊያን ተስፋ በመቁረጥ በሐዘን ተውጠው ታይተዋል።

ፕሬዚደንት ባሻር አል አሳድ ዕሁድ ዕለት ከሥልጣን መወገዳቸውን ተከትሎ በብዙ ሺህ የተቆጠሩ እስረኞች እጅግ አስከፊ ከሆነው ወህኒ ቤት ወጥተዋል። ለረጅም ጊዜ ደብዛቸው በመጥፋቱ ተገድለዋል ብለው ከደመደሙ ቤተሰቦቻቸው ጋር እያለቀሱ ሲገናኙ የታዩም አሉ።

ሌሎች ቁጥር ስፍር የሌላቸው ነዋሪዎች ደግሞ እጅግ በሚዘገንን ሁኒታ ቆሻሻ እና ጨለማ በሆነው ወህኒ ቤት ውስጥ ከዓመታት በፊት በተቃዋሚ ሰልፎች ላይ የታሠሩባቸውን ሰዎች መፈለጋቸው ቀጥለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG