በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ግዙፉን የድሆች ሰፈር አፈራርሳለች ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘ


ኬንያ ግዙፉን የድሆች ሰፈር መንገድ ለመሥራት አፈራርሳ ሰውን መኖሪያ አልባነት አድርጋለች ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዛት።

ኬንያ ግዙፉን የድሆች ሰፈር መንገድ ለመሥራት አፈራርሳ ሰውን መኖሪያ አልባነት አድርጋለች ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አወገዛት።

ዓለምቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አምነስቲ ዛሬ ጠዋት በሰፈሩ የሚገኝ ትምህርት ቤት ሲፈርስ የሚያሳይ ቪዲዮ በትዊተር አሰራጭቷል።

ዋና ከተማዋ ናይሮቢ ጠርዝ ላይ የሚገኘው ኪቤራ የሚባለው ቀበሌ ከአራት መቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች ሲሆን ከሰፈሩ የተወሰነው ክፍል የሚፈርሰው የከተማዋን የትራፊክ ጭንቅንቅ ለመቅረፍ የሚረዳ አዲስ መንገድ ለመገንባት መሆኑ ታውቋል።

ከአሁን ቀደም ለዚሁ ፕሮጄክት ከመንደሩ የተወሰነ ቦታ የፈረሰ ሲሆን መንግሥት በቀጣይነት ለሚፈርሱ ቤቶች አስቀድሞ ነዋሪውን እንደሚያስታውቅና ካሳም እንደሚከፍል ቃል ገብቶ ነበር። የትናንቱ የቤት ማፍረስ ዕርምጃ ግን ሳይነገራቸው በድንገት እንደተፈፀመ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

የኬንያ የከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ውንጀላውን አስተባብሎ አምነስቲን የገንዘብ መዋጮ ለመሰብሰብ ብላችሁ አትዋሹ ማለቱን የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG