በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከደራ ወረዳ ሲቪሎች በታጣቂዎች እንደታገቱ ተገለጸ


ከደራ ወረዳ ሲቪሎች በታጣቂዎች እንደታገቱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:33 0:00

ከደራ ወረዳ ሲቪሎች በታጣቂዎች እንደታገቱ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ፣ ከ15 ቀናት በፊት መደበኛ ነዋሪዎች በታጣቂዎች መታገታቸውንና እስከ አሁን ድረስ ያሉበት እንደማይታወቅ፣ ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አምስት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ባለፈው የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ወሰን ተሻግረው ወደ ወረዳዋ ሦስት ቀበሌዎች ገቡ ያሏቸው ታጣቂዎች፣ ነዋሪዎቹን አግተው እንደወሰዷቸው ተናግረዋል። በዕለቱ በነበረው የተኩስ ልውውጥም ሕይወት ማለፉንም አስተያየት ሰጪዎቹ አመልክተዋል። የዞኑ አስተዳዳሪ፣ “ጽንፈኛ” ሲሉ የጠሯቸው የፋኖ እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች

የሚንቀሳቀሱባቸው ቀበሌዎች እንደሆኑ ገልጸው፣ የእገታ ድርጊቱን ፈጻሚዎች ማንነት ለመለየት

“ከኅብረተሰቡ ጋራ እንሠራለን፤” ብለዋል። የአማራ ፋኖ በጎጃም ቃል አቀባይ መኾናቸውን የገለጹት ማርሸት ፀሐዩ በእንደዚህ ዓይነት እንቅስቃሴ አመለሳተፋቸውን ገልፀው መንግሥትን ኮንነዋል። በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ከተባለው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ታጣዊዎች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG