በደቡብ ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ አታዬ በሚባል ቀበሌ ውስጥ “ስምንት ሰላማዊ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል” ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ክሥ አሰምተዋል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ደግሞ “እርምጃ የተወሰደው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሳይሆን ወንጀል ፈፅመው በተደበቁና በመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች ላይ ተኩስ በከፈቱ ሽፍቶች ላይ ነው” ብለዋል።
“የተገደሉትም ስምንት ሳይሆኑ አራት መሆናቸውን” ተናግረው ሌሎች ሃያ ታጣቂዎችን ከነትጥቃቸው መያዛቸውን ገልፀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።