በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የተኩስ አቁም ጥሪያችንን እንቀጥላለን” - ኔድ ፕራይስ


ፎቶ ፋይል፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ
ፎቶ ፋይል፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ

ትናንት ማክሰኞ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በወጣው የሀገር መከላከይ ኃይሎችን ጨምሮ ሌሎችም የጸጥታ ኃይሎች በህወሓት ኃይል ላይ እርምጃ እንዲወስዱ አቅጣጫ አስቀምጠናል በሚል ባወጣው መግለጫ ላይ አስተያየታቸውን የተጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪያችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

የዩኤስኤድ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ተኩስ እንዲቆም ጥሪ አቅርበው በተመለሱ በአንድ ሳምንት ውስጥ የጦርነት ጥሪ መደረጉ ላይ አስተዳደርዎ ምን አስተያየት አለው ለሚለው ጥያቄ በሰጡት መልስ

"እኛ አሁንም ጥሪያችንን አጠንክረን እንቀጥላለን፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ይህንኑ ጥሪ ከሳቸው በግልጽ ሰምተውታል፣ ትኩረት መሰጥት ያለበት ሁሉን አቀፍ ሰላም እንዲሰፍን በይበልጥም ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ መከራ እንዲያበቃ ንግግር ማድረግ ላይ መሆን አለበት" ብለዋል።

ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ "ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ተነስቷል" ያለውን ኃይል ለመደምሰስ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለክልል ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች አቅጣጫ መቀመጡን አጽንኦት ሰጥቶ ዕድሜው የፈቀደ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሀጋሩን ለመጠበቅ ዘብ እንዲቆም ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ጦሩን ከትግራይ ክልል ያስወጣው ተሸንፎ እንጂ የተኩስ አቁም በማወጅ አይደለም በማለት የሚናገረው ህወሓትም፣ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ተቀባይነት እስካላገኙ ድረስ ውጊያውን እንደሚቀጥል በተለያዩ አመራሮቹ መግለጹ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG