በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤትና የአካባቢ ሥልጣናት ምርጫ

ከሁለት ሣምንታት በኋላ ለሚካሄዱት የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤትና የአካባቢ ሥልጣናት ምርጫ ቅስቀሣ የተሰበሰበውና እየዋለ ያለው ገንዘብ በሃገሪቱ የምርጫ ታሪክ እጅግ ከፍተኛው እንደሆነ ተገለፀ።

ከሁለት ሣምንታት በኋላ ለሚካሄዱት የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤትና የአካባቢ ሥልጣናት ምርጫ ቅስቀሣ የተሰበሰበውና እየዋለ ያለው ገንዘብ በሃገሪቱ የምርጫ ታሪክ እጅግ ከፍተኛው እንደሆነ ተገለፀ።

በገንዘብ አሰባሰብና አቅም የበላይነት እንደያዙ የሚነገርላቸው የዴሞክራቲክ ፓርቲው ዕጩዎች ለተራዘመ ጊዜ በሪፐብሊካን ፓርቲው የበላይነት የተያዘውን የተወካዮች ምክር ቤቱን የሕግ መምሪያና የሕግ ወመሰኛ አካላት መልሰው ለመቆጣጠር በብርቱ እየጣሩ መሆናቸው እየተነገረ ነው።

የምርጫው አዝማሚያ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ምንም እንኳ ሪፐብሊካኑ በሕግ ወመሰኛው ውስጥ አሁን ያላቸውን 51 ለ 49 የሆነ ጠባብ ልዩነት አስጠብቀው መቆየት ሳይችሉ አይቀሩም ቢባልም በሕግ መምሪያው ውስጥ ግን ይዞታውን ዴሞክራቶቹ ሳይገለብጡ እንደማይቀሩ እየተሰማ ነው።

ዴሞክራቲክ ፓርቲው የሕግ መምሪያውን ለመቆጣጠር አሁን የያዟቸውን መቀመጫዎች አስጠብቀው ቢያንስ 23 ዕጩዎቹዎቻቸው ተጨማሪ መቀመጫዎችን ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG