በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዴሞክራቶች የመድሃኒት ዋጋን ዝቅ በሚያደርገው እቅድ ተስማሙ


ሴነተር ጆ ማንሽን
ሴነተር ጆ ማንሽን

ዴሞክራቶች ከፕሬዚዳንት ጆባይደን የ1.75 ትሪሊዮን ዶላር እቅድ ውስጥ የመድሃኒት ዋጋን ለአረጋውያን ዜጎች መቀነስ ከሚያስችል ስምምነት መድረሳቸውን ተናገሩ፡፡

በህግ መወሰኛው ምክርቤት መሪ ቻክ ሹመር ትናንት በሰጡትመገለጫ እንዳስታወቁት ስምምነቱ ዜጎች ከኪሳቸው የሚያወጡት የሜዲኬድ ወጭ ከ2ሺዶላር እንዳይበልጥ የሚያደርግ ሲሆን የኢንሱሊን ዋጋም እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

ሌላው ከፍተኛ ቀረጥበመጣል የሚታወቁ ክፍለግዛቶችን ይነካል የተባለው፣ እስከ 10ሺ የሚደርሰው የክፍለግዛቶችና በወረዳዎች ያሉየቀረጥና ግብር ገደብንአስመልክቶ የተደረሰበት ስምምነትመሆኑን ተመልክቷል፡፡

ዴሞክራቶቹ የህግ ረቂቁንእስከ ነገ ሀሙስ ድረስ ለማጠናቀቅ ተስፋያደረጉ ሲሆን ዴሞክራቱ ሴነተር ጆ ማንሽን ድጋፋቸውን እንደሚሰጡት ጆ ባይደን ለጉባኤ ካሉበት አውሮፓ ሆነው ፍንጭ መስጠታቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG