በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ባይደን እና የዩናይትድ ስቴትስ ም/ቤት መሪዎች በብድር ጣሪያው ጉዳይ ዛሬ ይነጋገራሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ፣ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔው ኬቭን መካርቲ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ፣ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔው ኬቭን መካርቲ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የምክር ቤቱ ከፍተኛ ሪፐብሊካን እና ዲሞክራት መሪዎች እያወዛገበ ባለው የሀገሪቱ የብድር ጣሪያ ጉዳይ ዛሬ በዋይት ሀውስ ቤተ መንግሥት ይወያያሉ።

ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ሪፐብሊካን አባላት በኩል የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔው ኬቭን መካርቲ እና በመወሰኛ ምክር ቤቱ የውህዳን ሪፐብሊካኖች መሪው ሚች መካነል በስብሰባው ላይ ይገኛሉ። ከዲሞክራቶች በኩል ደግሞ የተወካዮች ምክር ቤት ዲሞክራቶች መሪው ሃኪም ጄፍሪ እና የመወሰኛ ምር ቤቱ ብዙሃን ዲሞክራቶች መሪ ሴኔተር ቸክ ሹመር እንደሚገኙ ታውቋል።

ሪፐብሊካኖች የመንግሥቱን የብድር ጣሪያ ለማሳደግ የምንስማማው መንግሥት ወጪዎቹን ከቀነሰ ነው በማለት አጥብቀው እየተከራከሩ ናቸው። ፕሬዚዳንት ባይደን በበኩላቸው "መንግሥት ዕዳውን የመክፈል ግዲታ ያለበት ከመሆኑም ሌላ ሁለቱ ጉዳዮች ለየብቻ መስተናገድ አለባቸው" በማለት በመሟገት ላይ ናቸው።

የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚንስትር ጃነት ዬለን እአአ በመጪው ሰኔ 1 ሲመጣ መንግሥት ዕዳዎቹን የሚከፍልበት በቂ ገንዘብ ላይኖረው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

XS
SM
MD
LG