በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዲሞክራቶች አምስተኛ ዙር ክርክር ይካሄዳል


እአአ 2020 በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የፓርቲያቸው ዕጩ ሆነው ለመመረጥ የሚፎካከሩት ዲሞክራቶች ዛሬ አምስተኛቸውን ክርክር ያካሄዳሉ።

በደቡባዊቱ የዩናይትድ ስቴትስ ጆርጂያ ክፍለ ግዛት አትላንታ ከተማ በሚከናወነው ክርክር የሚካፈሉት አስሩ ተፎካካሪዎች ብዛት ካላቸው ተፎካከሪዎች መካከል ጠንከር ብለው ብቅ ለማለት የሚሞክሩበት ይሆናል።

በሀገርቀፍ የህዝብ አስተያየት ግምገማዎች መደዳውን ግንባር ቀደሙን ቦታ ይዘው የቆዩት የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሴኔተር ኤሊዛቤት ዋረን እና ሴኔተር በርኒ ሳንደርስ በዛሬ ማታው ክርክር ይካፈላሉ።

በቅርቡ በአይዋ እና በኒው ሃምፕሽየር ክፍለ ግዛቶች የተካሄዱት የመራጮች ዝንባሌ ግምገማዎች የኢንዲያና ሳውዝ ቤንድ ከተማው ከንቲባ ፒት ቡቲጂጅን ከግንባር ቀደሞቹ ውስጥ ጨምረዋቸዋል።

ሁለቱ ክፍለ ግዛቶች የዕጩ መረጣ የሚካሄድባቸው የመጀመሪያዎች ቦታዎች ስለሚሆኑ በምርጫው ሂደት የጎላ ቦታ ይኖራቸዋል። የአይዋው የመረጣ ጉባኤዎች የካቲት ሶስት የኒው ሃምፕሻይሩ ቅድመ ምርጫ ደግሞ የካቲት 11 ይካሄዳል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG