ዛሬ ማክሰኞ ማታ በዲሞክራቲክ ፓርቲው ጉባኤ ዋና ተናጋሪ የሆኑት የቀድሞ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ለስምንት ዓመታት ምክትል ፕሬዚደንታቸው የነበሩትን ፕሬዚደንት ጆ ባይደንን አመስግነዋቸዋል።
"ጆ ባይደን በታሪክ ዲሞክራሲን እጅግ ከባድ ከሆነ አደጋ የተከላከሉግሩም ፕሬዚደንት ሆነው ይታወሳሉ" ብለዋል።
በኅዳር ወር የሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እጅግ ብርቱ ፉክክር የሚታይበት እንደሚሆን የተነበዩት ኦባማ ስለ ካማላ ሃሪስ የአቃቤ ሕግነት ተመክሮም በማንሳት "ካማላ ለሥራው ዝግጁ ናቸው" ሲሉ ተናግረውላቸዋል።
ከቀድሞው ፕሬዚደንት በፊት የተናገሩት ባለቢታቸው ሚሼል ኦባማም ከጉባኤተኛው በከፍተኛ ስሜት በጭብጨባ የደመቀ ንግግር አድርገዋል።
የአሜሪካ ህዝብ "ለፕሬዚደንትነት ከተወዳደሩ እጅግ የበቁ ዕጩዎች አንዷ" ሲሉ የገለጿቸውን ካማላ ሃሪስን እና ቲም ዎልዝን እንዲመርጥ የቀድሞይቱ ቀዳማዊት እመቤት ጥሪ አቅርበዋል።
መድረክ / ፎረም