በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዲሞክራት ፓርቲ አባላት ስለሚስጥራዊ ሰነዶች አያያዛቸው ባይደንን ተቹ


ዲሞክራቱ ሴናተር ዲክ ደርባን
ዲሞክራቱ ሴናተር ዲክ ደርባን

ምስጢራዊነታቸውን የሚያመለክቱ ምልክቶች ያሉባቸው ተጨማሪ ሰነዶች መገኘታቸውን ተከትሎ በርካታ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት በትናንትናው ዕለት በሰጡት አስተያየት የፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን የምስጢራዊ ሰነዶች አያያዝ ተቹ።

ከሲኤኔኤን ቴሌቭዥን ጣቢያ “ስቴት ኦፍ ዘ ኔሽን” ከተሰኘው ፕሮግራም ጋር ቃለ ምልልስ ባደርጉበት ወቅት በጉዳዩ ላይ ያላቸውን አስተያየት የተጠየቁት ዲሞክራቱ ሴናተር ዲክ ደርባን፣ ባይደን “በሁኔታው ሊያፍሩ ይገባል” ሲሉ ተችተዋል ።

“ባይደንም ሆኑ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሚስጥራዊ ሰነዶቹ ከእጃቸው ሊገኙ ባይገባም” ያሉት ደርባን አክለውም “ሆኖ የተገኘውም ሆነ እና የተከተለው ግን የሁለቱ በእጅጉ የተለያየ ነው” ብለዋል።

በባይደን የምክትል ፕሬዚዳንትነት ዘመን የተቀመጡ መሆናቸውን የሚጠቁሙ “ምስጢራዊ” በሚል የተለዩ ሰነዶች በዋሽንግተን ዲሲው የፔን ባይደን የጥናት ማከል የቀድሞ ጽ/ቤታቸው ከተገኙት ወዲህ ከመኖሪያ ቤታቸው ተጨማሪ ስድስት ምስጢራዊ ሰነዶች

መገኘታቸውን እና ኤፍቢአይ መውሰዱን የባይደን የሕግ አማካሪ ባለፈው ቅዳሜ በሰጡት አስተያየት አመልክተዋል።

በሌላ ተያያዥ ርዕስ ትረምፕ የሥልጣን ዘመናቸው እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2021 መጀመሪያ ካበቃ በኋላ “ምስጢራዊ” መሆናቸው ተለይቶ የተቀመጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰነዶችን ወደ መኖሪያ ቤታቸው መውሰዳቸውን እና ሰነዶቹን እንዲመልሱ በመንግስት የቀረበላቸውን ጥያቄ ያለመቀበላቸውን ተከትሎ የፍርድ ቤት የፍተሻ ማዘዣ እንደወጣባቸው የፍትህ ሚንስቴር አስረድቷል።

“ሁለቱም ቢሆኑ መከሰታቸው አሳዛኝ ነው።” ያሉት ሴናተር ደርባን “ይሁንና በቀድሞው ፕሬዚዳንት እና ባሁኑ ፕሬዚዳንት እጉዳዩ የሰጧቸው ምላሾች ከዚህ በላይ የተራራቁ ሊሆኑ አይችሉም።” ብለዋል።

ባደን በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ ጉዳዩን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ ቡድናቸው “በጣት የሚቆጠሩ” ያሏቸውን ሰነዶች ከተሳሳተ ሥፍራ ተቀምጠው ማግኘቱን እና ወዲያውኑም ለሚመለከታቸው ክፍሎች ማስረከቡን መናገራቸው ይታወሳል።

ሌላው ከዲሞክራት ፓርቲው ወገን የሆኑት የእንደራሴዎች ምክር ቤት አባሉ ሴናተር ጆ ማንሺን በበኩላቸው ትናንት እሁድ ለኤንቢሲው “ሚት ዘ ፕሬስ” የተሰኘ ፕሮግራም ሲናገሩ፣ ባይደንም ሆኑ ትረምፕ ሁለቱም እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸው ለማመን የሚያዳግት ቢሆንም፣ ለፍርድ ከመቸኮላችን አስቀድሞ ግን የተሰየሙት ልዩ

መርማሪዎች እያደረጓቸው ያሏቸው ምራዎች መጠናቀቅ አለባቸው።” ብለዋል።

"አንዱ ከሌላው የበለጠ ጎጂ ነበር? .. ሁለቱም አንድ ናቸው? .. አንዱ ምንም ዓይነት ችግር አልፈጠረም ወይንም ደግሞ አንዱ ከሌላው የበለጠ ቸልተኝነት እና ኃላፊነት የጎደለው ነበር? የሚሉት እኔ የምመልሳቸው ጥያቄዎች አይደሉም።” ያሉት ማንሺን “ልዩ መርማሪዎቹ ከፖለቲከኞች እና ከሚከተለው የፖለቲካ ጫወታ የተሻለ ሥራ ይሰራሉ ብዬ አስባለሁ።” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG