በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዲሞክራቶች ክርክር


በዩናይትድ ስቴትስ በመጪው ዓመት በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት ትረምፕን ለማሸነፍ የምርጭ ዘመቻ በማካሄድ ላይ የሉት 12 ዲሞክራት ተወዳዳሪዎች ትናንት ማታ የሞቀ ክርክር አካሂደዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዲሞክራት አባላት በፕሬዚዳንቱ ላይ የምክር ቤት ክስ ለመመስረት የሚያስችል በደል ፈፅመው እንደሆነ ለማጣራት እየሞከሩ መሆናቸው ይታወቃል።

ሁሉም ዲሞክራት ተወዳዳሪዎች ለአራት ሳምንታት ያህል በመካሄድ ላይ ያለውን የክስ ምርመራ ይደግፋሉ። ትረምፕ ዲሞክራቶች በሚበዙበት የተወካዮች ምክር ቤት መከሰስ አለባቸው የሚሉብትን ምክንያት በቴሌቪዥን ሲታይ በነበረው ክርክራቸው ዘርዝረዋል።

በውድድሩ እየመሩ ያሉት የቀድሞ ምክትል ፕረዚዳንት ጆ ባይደን “እኚህ ፕሬዚዳንት በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሙሰኛ ናቸው” ብለዋል። በክርክሩ የተሳተፉት ተወዳዳሪዎች ሁሉ አስተጋብተውታል።

በምርጫው ዘመቻ ብዙ ድምፅ እያገኙ ያሉት ሌላዋ ተወዳዳሪ የማሳቹሰትስ ተወካይ ሴኔተር ኤሊዝበት ዋረን ዶናልድ ትረምፕ ህግን ጥሰዋል። ማንም ከህግ በላይ ሊሆን ስለማይችል መከሰስ አለባቸወ ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG