በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲሞክራሲ በተግባር


የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነሐሴ 2 ቀን 2009 ዓ.ም የተካሄደውን ፕሬዘደንታዊ ምርጫ ውጤት ውድቅ አድርጎ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ባለፈው ሣምንት ማዘዙ ይታወቃል።

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነሐሴ 2 ቀን 2009 ዓ.ም የተካሄደውን ፕሬዘደንታዊ ምርጫ ውጤት ውድቅ አድርጎ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ባለፈው ሣምንት ማዘዙ ይታወቃል። በዚያ መላ ሀገሪቱን ባስደነገጠ የፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት በምርጫው ማሸነፋቸው የታወጀው የወቅቱ ፕሬዘዳንት ኦሁሩ ኬንያታ በ60 ቀናት ውስጥ ከዋና የፖለቲካ ተቀናቃኛቸው ከራይል ኦዲንጋ ጋር እንደገና ለሥልጣን ይወዳደራሉ፡፡

ኦዲንጋ ምርጫው እንዲሠረዝ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ያስገቡት ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታን እንዲረዳ ተደርጎ ተጭበርብሯል በሚል ሲሆን፣ ነጻው የምርጫና ድንበር ኮሚሽንም እንዲፈርስ ጠይቀዋል።

አንድ ፍርድ ቤት የፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ውጤት ሲሰርዝና አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ሲወስን ብቻ ሳይሆን ፕሬዘዳንቱም ብይኑን ሲቀበሉ በአፍሪካ ፖለቲካ ታሪክ የመጀመሪያው ነው።

ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ከዚህ ምን መማር ይችላሉ?

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ዲሞክራሲ በተግባር
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:09 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG