በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲሞክራሲ በተግባር

“ባለፈው ዓመት ከሩሲያ ጠበቃ ጋር የተደረገውን ግንኙነት በተመለከተ ወንድ ልጃቸው ዶናልድ ጁኒየር ለኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የሰጠውን አስተያየት በግል አዘጋጅተውና ቃል በቃል እንዲፅፍ አድርገው ያቀረቡለት አባትየው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው።

“ባለፈው ዓመት ከሩሲያ ጠበቃ ጋር የተደረገውን ግንኙነት በተመለከተ ወንድ ልጃቸው ዶናልድ ጁኒየር ለኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የሰጠውን አስተያየት በግል አዘጋጅተውና ቃል በቃል እንዲፅፍ አድርገው ያቀረቡለት አባትየው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ናቸው።

በፕሬዚዳንቱ የተቀነባበረው መልስም

“በግንኙነቱ ወቅት ውይይት የተደረገው በሩሲያ ሕፃናት የጉዲፈቻ ፕሮግራም ላይ ነው” የሚል ነው።

ቀደም ሲል ልጃቸው የተለዋወጧቸው የኢሜይል መልዕክቶች በተቃራኒው ግን ከሩሲያው ጠበቃ ጋር የተደረገው ግንኙነት ዋና ዓላማ የሂላሪ ክሊንተንን ምረጡኝ ዘመቻ መጉዳት የሚያስችሉ መረጃዎች ለማግኘት ቃል የተገባላቸው መሆኑን ያሳያሉ።

ከትላንት በስቲያ ሰኞ ይህን ከባድና አጋላጭ የምርምር ዘገባ ያቀረበው ዘ ዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ነው።

ቀጣዩ “ዲሞክራሲ በተግባር” ፕሮግራም የሰሞኑን የዋይት ኃውስ የካቢኔ ሹም ሽር እና አለ የሚባለውን አስተዳደራዊ ትርምስ በባለሞያ ያስተነትናል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ዲሞክራሲ በተግባር
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:41 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG