በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲሞክራሲ በተግባር


የካታርን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ከአጨቃጫቂው ራስ ዱሜራ የድንበር አካባቢ መልቀቅ ተከትሎ አካባቢውን ለመቆጣጠር ኤርትራ ወታደሮቿን አስፍራለች ስትል ጂቡቲ ከስሳለች።

የካታርን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ከአጨቃጫቂው ራስ ዱሜራ የድንበር አካባቢ መልቀቅ ተከትሎ አካባቢውን ለመቆጣጠር ኤርትራ ወታደሮቿን አስፍራለች ስትል ጂቡቲ ከስሳለች።

ሁለቱ ሃገሮች የመሬት ውዝግቡን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥሪ አስተላልፏል።

ፈታሽ ቡድን ወደ ሁለቱ ሃገሮች እንዲላክም በአፍሪካ ኅብረት የቀረበውን ሃሳብ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አባላት መደገፋቸውም ተገልጿል።

ካታር 450 አቃቢያነ-ሰላም ወታደሮቿን ኤርትራና ጅቡቲ ድንበር ያነሣችው ሁለቱ ሃገሮች ከዶሃ ጋር ዲፕሎማሲ ቁርቁስ ውስጥ ከገባችው ከሳዑዲ አረቢያ ጎን ቆመዋል በሚል እንደነበር ይታወሣል።

በጂቡቲና በኤርትራ መካከል ያገረሸው አለመግባባት ባካባቢው ሀገሮች ላይ ምን እንደምታ ይኖረዋል?

የምሽቱ “ዲሞክራሲ በተግባር” ፕሮግራም ፡ የባለሞያ ትንታኔም ይዟል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዲሞክራሲ በተግባር
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:18 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG