የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ በምዕራቡ ግዛት በቤንሻንጉል ግዙፍ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ ለመሥራት ማቀዱን አስታውቋል። በዓባይ ወንዝ ላይ ሊሠራ የታቀደው ግድብ ከሱዳን ድንበር 40 ኪሎ ሜትር የሚርቅ ሲሆን ወጪውም ከ 80 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ተገልጿል። ያላንዳች የባዕድ ሀገር ዕርዳታ ግንባታው ይጠናቀቃል የተባለው የሚለንየሙ ግድብ 5,200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመነጭና ግንባታው ከአምስት እስከ አሥር ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል ተነግሯል።
በሙያ የኢኰኖሚ ምሁር የሆኑት ዶክተር ጌታቸው በጋሻው በዩናይትድ ስቴትስ ቺካጐ ሀርፐር ኮሌጅ ያስተምራሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ጽሁፍ አቅርበዋል። ውይይቱን ያዳምጡ
የግንባታ እቅዱም ያልተመከረበትና በጥድፊያ የተወጠነ ነው ይላሉ ዶ/ር ጌታቸው በጋሻው