ምርጫ ቦርድ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ በመጭው ጥር 29/2015 ዓ.ም እንደሚያሄድ ትናንት ማምሻው ላይ ባጠናቀቀው ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተካሄደ ምክክር አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ጥር 29/2015 ዓ.ም ህዝበ ውሳኔ እንደሚካሔድ አስታወቀ፡፡
ቁጥሩ ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚገመት መራጭ ድምፅን ለመስጠት ይመዘገባል የሚል ግምት እንዳለው ያስታወቀው የምርጫ ቦርድ፣ ለህዝበ ውሳኔው ማስፈፀሚያ የሚውል ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚጠይቅም አመልክቷል።
ቦርዱ የህዝበ ውሳኔ ዕቅዱን ለባለድርሻ አካላት ባስተዋወቀበት በዚህ መድረክ የተሳተፉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በምርጫ አስፈፃሚዎች ገለልተኝነት፣ በፀጥታ ሁኔታ እና በህዝበ ውሳኔው ዲሞክራሲያዊነት ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና ምክትል ሰብሳቢው ውብሸት አየለ ለፓርቲዎቹ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]