በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማሩ ሂደት ጀምሯል


የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ለታ ተስፋዬ
የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ለታ ተስፋዬ

በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ያለፋቸውን የትምህርት ክፍለ-ጊዜ ለማካካስ ዩኒቨርሲቲው ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ገለፁ።

ተማሪዎቹ ከተቋረጠ ከወር በላይ የሆነው የኢንተርኔትና ስልክ አገልግሎት እንዲመለስላቸውም ጠይቀዋል።

የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ለታ ተስፋዬ “ዩኒቨርሲቲው ወደ ቀድሞ መረጋጋቱ ተመልሶ በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን ለማስመረቅ እየሰራን ነው” ብለዋል።

ታገቱ የተባሉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ጉዳይ በተመለከተም “ተማሪዎቹን የማፈላለግ ጥረት ቀጥሏል፣ ተገኝተው ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እየሰራን ነው" ብለዋል።

ታገቱ የተባሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ይገኙ አይገኙ እስካሁን ከቤተሰብም ሆነ ከመንግሥት የተሰጠ መግለጫ የለም።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማሩ ሂደት ጀምሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:30 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG