በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የካሽሚርን ውዝግብ እንዲሸመግሉ ፕሬዚዳንት ትረምፕን አልጠየቅሁም" - ህንድ


የካሽሚርን ውዝግብ እንዲሸመግሉ ፕሬዚዳንት ትረምፕን አልጠየቅሁም ስትል ህንድ አስታወቀች። ይሁንና ዋይት ኃውስ ኒው ዴልሂ እና ኢስላማባድ በካሽሚር ምክንያት ያላቸውን የቆየ ውዝግብ እንዲሸመግሉ ፕሬዚዳንት ትረምፕ በህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር መጠየቃቸውን አመልክቷል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ “ተጠይቄያለሁ” ያሉት ነገር እውነት ስለመሆኑ ለቀረበ ጥያቄ፣ የኢኮኖሚክስ ምክር ቤት ዳይሬክተሩ ላሪይ ኩደሎው ሲመልሱ፣ “ፕሬዚዳንቱ በሬ ወለደ ነገር አያውቁበትም” ካሉ በኋላ፣ የጋዜጠኛውን ጥያቄም “በጣም ብልግና” ብለውታል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ የካሽሚርን ውዝግብ ለመሸምገል ፍላጎት ከማሳየታቸውም አስቀድሞ ግን፣ ፓኪስታን የርሳቸውን ሽምግልና ትሻው እንደነበር ይታወቃል።

ለማንኛውም የፕሬዚዳንት ትረምፕ የተጠይቄያለሁ አነጋገር፤ ህንድ ውስጥ ውዥንብር መፍጠሩ ተሰምቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG