በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡድን ሰባት /ጂ7/ መሪዎች ጉባዔ


የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የአፍሪካ ልማት ባንክ በአፍሪካ ሴቶች የሚካሂዱ የንግድ ሥራዎችን ለማሳደግ የታለመ የሦስት መቶ ሚሊዮን ዶላር መርሃ ግብር ይፋ አድርገዋል።

የቡድን ሰባት ጂ7 መሪዎች ጉባዔ በተካሄደባት በፈረንሳይዋ ቢያሪትዝ ከተማ ይፋ የሆነው ዕቅድ በአህጉሪቱ ዙሪያ በንግድ ሥራ የተሰማሩ ሴቶች የብድር ተደራሽነታቸው በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ከፍ ለማደግ የታለመ እንደሆነ ተገልጿል።

መርሃ ግብሩን ስታስተዋውቅ የቆየችው የተመድ የህፃናት መርጃ ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደሯ የበኒንዋ ታዊቅ ድምፃዊ አንጀሊክ ኪጆ ከፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ጋር ሆና ፕሮጄክቱን በማስተባበር ቁልፍ ሚና መጫወቷ ተዘግቧል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ እንደሚናገረው ሰባ ሰባት ከመቶ የአፍሪካ ሴቶች በፋይናንስ ፈርፍ ተጠቃሚነት ዕድል የላቸውም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG