በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደብረ ታቦር ከተማ ላይ በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ ሲቪሎች ተገደሉ


ደብረ ታቦር
ደብረ ታቦር

ደብረ ታቦር ከተማ ላይ ትናንት የተተኮሰ ከባድ መሳሪያ ሲቪሎችን መግደሉንና በከተማው ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ላይም ዛሬ ድብደባ መፈፀሙን የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪና የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል።

የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ ዛሬ የተተኮሱት ከባድ መሳሪያዎች በአርሶ አደር መንደሮች ላይ መውደቃቸውና የደረሰውን ጉዳት በውል እንደማያውቁ ተናግረዋል።

ጥቃቱን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ከደብረ ታቦር ከተማ ወደ አጎራባች ወረዳዎችና ቀበሌዎች የሚፈናቀለው ሰው ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተሰምቷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

ደብረ ታቦር ከተማ ላይ በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ ሲቪሎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:00 0:00


XS
SM
MD
LG