በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የነገይቱ ኢትዮጵያ መጭ ጊዜያት በመንታ መነፅሮች ሲቃኝ


ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ እና ዶ/ር ዮናስ ብሩ
ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ እና ዶ/ር ዮናስ ብሩ

“..ኢትዮጵያ ዛሬ በጠርዝ ያለች አገርናት::.." ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ:: ".. እርግጥምክኒያተ-ብዙ ፈተናዎች የተደቀኑባት አገር ብትሆንም የሚያስፈልጋት ግን የሂደት ማስተካከያ ነው::" ዶ/ር ዮናስ ብሩ::

የዛሬይቱን ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ አያያዝ በመርመር መቀጣዩ ምዕራፍ "ሊሆን ይገባዋል" ያሉትን በማስፈር የለውጡን አቅጣጫ በየበኩላቸው የቃኙ ሁለት የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት አዋቂዎች ናቸው በቅርቡ ይፋ ያደረጓቸውን ፅሁፎች መሠረት ባደረገ ዝግጅት የሚከራከሩት::

የመጀመሪያው ፀሃፊ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ የአፍሪቃ የስትራተጂያዊና የፀጥታ ጉዳዮች ተቁዋም ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ናቸው:: በቀደመው ወታደራዊ መንግሥት በሲቪል አስተዳደር እና በወታደራዊ ሞያ በተለያዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶች አገልግለዋል::

ሁለተኛውፀሃፊዶ/ር ዮናስ ብሩ በዓለም ባንክ ዓለም አቀፍ የንፅፅር ፕሮግራም ምክትል ሥራ አስኪያጅ በመሆን ያገለገሉ አንጋፋ የምጣኔ ኃብት ባለሞያ ናቸው:: በአምስት ቋንቋዎች በየሶስት ወሩ የሚታተመው የዓለም ባንክ የጥናት መፅሄት ዋና አዘጋጅ በመሆንም አገልግለዋል:: በቅርቡም ኢትዮጵያ ለምን ገለልተኛ የምጣኔ ሃብት አማካሪዎች መማክርት ማቋቋም እንደሚያስፈልጋት የሚሞግት አንድ ጥናታዊ ሰነድ ከሌሎች የሞያ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በተባባሪነት አዘጋጅተዋል::

የክርክራቸውን ፍሬ ነገሮች ከዚህ ይከታተሉ::

የነገይቱ ኢትዮጵያ መጭ ጊዜያት መንታ መነፅሮች - ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:09 0:00
የነገይቱ ኢትዮጵያ መጭ ዕጣ ሲቃኝ
please wait

No media source currently available

0:00 0:25:33 0:00
የነገይቱ ኢትዮጵያ መጭ ጊዜያት በመንታ መነፅሮች ሲቃኝ
please wait

No media source currently available

0:00 0:18:23 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG