በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ በጎርፍ የሞተው ቁጥር እያሻቀበ ነው


በጎርፍ አደጋ ነዋሪዎች መንገዱን አቋርጠው እየሸሹ
በጎርፍ አደጋ ነዋሪዎች መንገዱን አቋርጠው እየሸሹ

ኬንያ ውስጥ የጎርፍ አደጋ ሟቾች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተነግሯል።

ባለፈው ሃሙስ ላይ የሞላውን ሙኦኒ ወንዝን ለመሻገር ሲሞክሩ የነበሩ ስምንት ሰዎች ሰጥመው መሞታቸው ተነግሯል።

እስካሁን የሦስት ሰዎች አስከሬን መገኘቱን የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የረድዔት ድርጅቶች “በአካባቢው ብዙም ያልተለመደ” ያሉትን መጥለቅለቅ ያስከተለው ከባድ ዝናብ በብዙ የአፍሪካ ቀንድ ሃገሮች ውስጥ አሁንም ቀጥሏል።

አንዳንድ የመሠረተ ልማት አውታሮች በጎርፉ በከፊል መወሰዳቸውና መንደሮች መጥለቅለቃቸው ተዘግቧል።

ካለፈው መስከረም 20 አንስቶ በአፍሪካ ቀንድ የተለያዩ አካባቢዎች ጎርፍ ከመቶ በላይ ሰው መግደሉን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳቶች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ጎርፉ በተጨማሪም ከ700 ሺህ በላይ የሚሆን ሰው ሰው ማፈናቀሉንም የመንግሥታቱ ድርጅት አክሎ ገልጧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG