በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ6ሚሊዮን ማለፉ ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ የመቃብር ቆፋሪዎች በኮቪድ-19 የሞተውን ሰው ሬሳ ሳጥን ተሽክመው ለቀብር ሲጓዙ ቤካሲ፣ ኢንዶኔዢያ ነሐሴ 10/2021
ፎቶ ፋይል፦ የመቃብር ቆፋሪዎች በኮቪድ-19 የሞተውን ሰው ሬሳ ሳጥን ተሽክመው ለቀብር ሲጓዙ ቤካሲ፣ ኢንዶኔዢያ ነሐሴ 10/2021

በኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች ቁጥር ከስድስት ሚሊዮን ማለፉ ከዩናይትድ ስቴትሱ የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ መረጃ ማዕከል የተገኘው አሃዝ ጠቆመ።

በበሽታው የተነሳ ለህልፈት የተዳረጉት ቁጥር ስድስት ሚሊዮን ስድስት ሺህ ሰባት መቶ አርባ ስምንት መድረሱን ነው መረጃው ያሳየው። ይህ ታዲያ ሰዎች የአፍንጫ እና የአፍ መሸፈኛ ጭንብል መጠቀም እያቆሙ ባሉበት፣ ከቦታ ወደ ቦታ መጓዝ በቀጠለበትና በዓለም ዙሪያ ተዘግተው የነበሩ የንግድ ድርጅቶች እየተከፈቱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የወረርሽኙን ጋብ ያለማለት ባህሪ የሚያስታውስ መሆኑ ተመልክቷል።

ትናንት ሰኞ በሆፕኪንስ ማዕከል የተረጋገጠው አሃዝ በተጨባጭ ካለው የበሽታው ሰለባዎች አሃዝ በስፋት የሚያንስ እንደሆነ ይጠረጠራል። ሦስተኛ ዓመቱን የያዘው ዓለም አቀፍ ወረርሺኝ ገና እንዳልተወገደ የሚጠቁም መሆኑ ነው የተገለጸው።

ደቡብ አፍሪካ በተለይ በወረርሺኙ በከፋ ሁኔታ እንደተጠቃች ያወሳው ዘገባው ወረርሺኙ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ከሦስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝቧ በቫይረሱ ተይዞባታል። ከዘጠና ዘጠኝ ሽህ አምስት መቶ በላይ ለህልፈት ተዳርገዋል።

በአጠቃላይ መያዙ መዝገብ ላይ የሰፈረው ሰው ቁጥር ከአራት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን በላይ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG