ዶዋላ በተሰኘችና የካሜሩን የንግድ ማዕከል በኾነች ከተማ፣ አንድ ሕንጻ ተደርምሶ፣ እስከ አሁን 33 ሰዎች እንደሞቱ ሲታወቅ፣ 21 የሚኾኑቱ ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ሲሉ፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።
ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ሌሊት፣ በሌላ የመኖሪያ ሕንጻ ላይ እንደወቀደ ከታወቀው ባለአራት ፎቁ ሕንጻ ፍርስራሽ ሥር፣ ዛሬ ሰኞ በሕይወት የተረፉ ሰዎች ይኖሩ እንደኹ ለማግኘት፣ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ፍለጋ ላይ ናቸው።
እ.አ.አ በ2016፣ በተመሳሳይ ኹኔታ በደረሰ አደጋ፣ አምስት ሰዎች እንደሞቱ ሲታወስ፣ ይህም በግንባታ ደንቦች መጣስ እና ደካማ የጥገና ሥራዎች ምክንያት መድረሱን፣ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
ተደጋጋሚውን የሕንጻዎች መደርመስ አደጋ ተከትሎ፣ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ፖል ቢያ፣ በከተማዪቱ፣ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ሕንጻዎች እንዲፈርሱ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።
መድረክ / ፎረም