በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጊኒ ዋና ከተማ የደረሰው ፍንዳታ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት አስከተለ


በጊኒ ዋና ከተማ ኮናክሪ የነዳጅ ማከማቻ ላይ ፍንዳታ ከደረሰ በኋላ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ለማጥፋት እየሰሩ እአአ ታኅሥስ 18/2023
በጊኒ ዋና ከተማ ኮናክሪ የነዳጅ ማከማቻ ላይ ፍንዳታ ከደረሰ በኋላ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እሳቱን ለማጥፋት እየሰሩ እአአ ታኅሥስ 18/2023

በጊኒ ዋና ከተማ ኮናክሪ በሀገሪቱ ዋና የነዳጅ ማከማቻ ላይ ባላፈው ሰኞ የደረሰውን ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ ነዋሪዎች ለከፍተኛ የትራንስፖርት ወጪ መጋለጣቸው ተነገረ፡፡

የ18 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው እና ከ200 በላይ የሚሆኑትን ለአካል ጉዳት የዳረገው ይህ ክስተት የከተማዋን የነዳጅ አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ አቋርጧል።

ፍንዳታው ባስከተለው የነዳጅ እጥረት በህዝብ ማመላለሻ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተመልክቷል፡፡

በፍንዳታው ሳቢያ 5 ዶላር ያህል የነበረው የትራንስፖርት ዋጋ በአንድ ጊዜ ወደ 32 ዶላር ከፍ ማለቱን ነዋሪዎችን የጠቀሰው የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

የመንግሥት ቃል አቀባይ ኦስማኔ ጓውል ዲያሎ ቃጠሎው 738 አባወራዎችን ለጉዳት መዳረጉን ተናግረዋል፡፡

በፍንዳታ ሳቢያ የተነሳው ቃጠሎ ለ24 ሰዓታት ያህል ሳይጠፋ የቆየ ሲሆን ሴኔጋል እና ማሊን ጨምሮ ጎረቤት ሀገራት የእሳት አደጋ መከላከል ቡድኖቻቸውን ወደ ስፍራው መላካቸውን ተዘግቧል፡፤

መንግስት የፍንዳታው መንስኤ ምን እንደሆነ በማጣራት ላይ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG