በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን ካቡል መስጊድ ላይ በደረሰ አጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ሃያ ሰዎች ተገደሉ

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በሚገኛ የሺያዎች መስጊድ ላይ በደረሰ አጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ቢያንስ ሃያ ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለፁ። በዓርብ የፀሎት ሰዓት ላይ በደረሰው ጥቃት የተገደሉት ሁለቱ ፖሊሶች ሲሆኑ ከአርባ በላይ መቁሰላቸው ታውቋል።

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በሚገኛ የሺያዎች መስጊድ ላይ በደረሰ አጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ቢያንስ ሃያ ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገለፁ። በዓርብ የፀሎት ሰዓት ላይ በደረሰው ጥቃት የተገደሉት ሁለቱ ፖሊሶች ሲሆኑ ከአርባ በላይ መቁሰላቸው ታውቋል።

የአፍጋኒስታን የአገር አስተዳደር ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናጂብ ዳኒሽ ኢማም ዛማን መስጊድ በራፍ ላይ ቢያንስ አንድ አጥቂ ቦምቡን ሲያፈነዳ ሌሎቹ ወደውስጥ ገብተው ጥቃት ማድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

“የእስልምና መንግሥት” ብሎ ራሱን የሚጠራው ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል።

ኢማ ዛማን ዓርብ ዓርብ ብዙ ምዓመናን ከሚገኙባቸው የአካባቢው ትላልቅ መስጊዶች አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ የዛሬው ጥቃት የደረሰው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትት ዶናልድ ትረምፕ አፍጋኒስታንን በተመለከተ አስተዳደራቸው የሚከተለውን አዲስ ፖሊሲ ይፋ ካደረጉ ከጥቂት ቀናት በኋላ መሆኑ ነው።

ፕሬዚደንቱ በአዲሱ ፖሊሲያቸው ለጦር ኃይል አዛዦቻቸው ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ሰጥተዋል። ፓኪስታንንም ባህሪዋን በአስቸኳይ መቀየርና ለአፍጋን ታሊባኖች መጠለያ መስጠትዋን ማቆም አለባት ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የአፍጋኒስታንንም መንግሥት ከዩናይትድ ስትቴትስ የሚያገኘውን እርዳታ አይነካብኝም ከሚል ስሜት ተቆጥቦ፣ የለውጥ እርምጃዎችን አፋጥኖ እንዲወስድ አሳስበዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG