በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ በኢቦላ ወረርሽኝ የ19 ሰዎች ህይወት አለፈ


ዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ ውስጥ የኢቦላ ወረርሽኝ ዳግም ተከስቶ ለ19 ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን፣ የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ።

ዴሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ ውስጥ የኢቦላ ወረርሽኝ ዳግም ተከስቶ ለ19 ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን፣ የዓለም ጤና ድርጅት ይፋ አደረገ።

ድርጅቱ ዛሬ እንዳስታወቀው፣ በሰሜናዊ ምዕራብ ኢኳተር ክፍለ ሀገር ውስጥ 39 ሰዎች ህመሙ እንዳለባቸው ታውቋል። ከእነዚህ መካከል 3 የጤና ጥበቃው ማዕከል ሠራተኞችም ይገኙባቸዋል።

የኮንጎ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ፣ እነዚህን በህመሙ የተያዙ ሰዎች አድራሻ እየፈለጉ የኢቦላ ክትባት ሙከራ በመስጠት ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።

ይህ RVSV-ZEBOV በመባል የሚታወቀው ክልባት በአውሮፓ፣ በአፍሪካና በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኙ ብዙ ሺህ ህሙማን ላይ ተሞክሮ፣ አስተማማኝነቱ ተመስክሮለታል።

የኪንታሮት ትኩሳት የሚያስነሳው የኢቦላ ቫይረስ የሚተላለፈው፣ ህመሙ ካለበት ሰው ወይም እንሰሳ ሰውነት ውስጥ በሚወጣ የፈሳሽ ግንኙነት ነው።

ትናንት እሑድ፣ የዓለም ጤና ድርጅት የልዑካን ቡድን፣ የድርጅቱን ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገ/ኢየሱስን ጨምሮ፣ በአሁኑ ወቅት ህመሙ ያገረሸባትን የኮንጎዋን ቢኮሮ ከተማ መጎብኘቱም ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG