በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞችን የያዘ ጀልባ ተገልብጦ 2 ሞቱ

ፎቶ ፋይል፦ በደቡባዊ ግሪክ በኪቲራ ደሴት ላይ ፍልሰተኞችን የጫና ጀልባ ከቋጥኝ ጋር በመጋጨቱ በርካቶች ሞተዋል፤ አስከሬኖቹም ከበርካታ ቀናት በኋላ ተንሳፋው ታይተዋል፡2/7/2022
ፎቶ ፋይል፦ በደቡባዊ ግሪክ በኪቲራ ደሴት ላይ ፍልሰተኞችን የጫና ጀልባ ከቋጥኝ ጋር በመጋጨቱ በርካቶች ሞተዋል፤ አስከሬኖቹም ከበርካታ ቀናት በኋላ ተንሳፋው ታይተዋል፡2/7/2022

ከመጠን በላይ ስደተኞችን የጫነ ጀልባ በስተምሥራቅ ግሪክ ባህር ዳርቻ አቅራቢያ ዛሬ ሰምጦ ቢያንስ 2 ፍልሰተኞች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

የግሪክ የባህር ድንበር ጠባቂዎች 24 ሰዎችን ማዳናቸውን አስታውቀው፣ አንድ ወንድና ሴት ግን ሞተው መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ ጀልባው 27 ሰዎችን ጭኖ የነበረ ሲሆን፣ አንድ ሰው የደረሰበት አለመታወቁ ተገልጿል፡፡

የፍልሰተኞቹ ዜግነት ለግዜው አልታወቀም፡፡

ከፕላስቲክ የተሠራውና ከመጠን በላይ የጫነው ጀልባ ከቱርክ ሳይነሳ እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡

XS
SM
MD
LG