በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞቃዲሾ አጥፍቶ ጠፊ ባደረሰው ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ ደረሰ


አንድ አጥፍቶ ጠፊ ዛሬ ሞቃዲሾ በሚገኝ የምዕራባውያን ወታደራዊ ካምዮን ላይ መኪና ነድቶ በመግጨቱ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ አራት ቆስለዋል።

አንድ አጥፍቶ ጠፊ ዛሬ ሞቃዲሾ በሚገኝ የምዕራባውያን ወታደራዊ ካምዮን ላይ መኪና ነድቶ በመግጨቱ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ አራት ቆስለዋል።

አጥፍቶ ጠፊው የነዳው መኪና በፈንጂዎች የተሞላ እንደነበርና የመታው ብረት ለበስ ወታደራዊ መኪና የጣልያን ወታደራዊ ኃይል መሆኑ ታውቋል። የጣልያን ወታደራዊ ኃይል የሚገኘው በሶማልያ መዲና ጃሌ ሲያድ ወታደራዉ ሰፈር ላይ ነው።

አል ሸባብ ወዲያውኑ ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል።

በፍንዳታው የተገደሉት ሁለቱ ወንዶች ሲሆኑ ከቆስሉት አራት ሰዎች መካከል አንድ ልጅና አንዲት ሴት እንድሚገኙባቸው ባለሥልጣኖችና ዕማኞች ተናግረዋል። ጣልያኖቹ ወታደሮች ጉዳት የደረሰበት ይኖር እንዳሆነ አልታወቀም። ጥቂት የጣልያን ወደታደሮች የሶማሊ መንግሥት ኃይሎችን ለማሰልጣን ሞቃዲሾ የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ወታደራዊ ተልዕኮ አካል ሆነው ይሰራሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG