በጣልያን ግዛት ሲሲሊ ፓሌርሞ ወደብ አቅራቢያ ከባህር ስትቀዝፍ የነበረች አንዲት ቅንጡ ጀልባ ዛሬ ሰኞ በመገልበጧ በውስጧ ከነበሩ ቱሪስቶች መካከል አንድ ሰው ሲሞት 6 ሰዎች የገቡበት አልታወቀም፡፡
የነፍስ አንድ ሠራተኞች የአንድ ዓመት ህጻንን ጨምሮ የ15 ተሳፋሪዎችን ህይወት ማትረፍ እንደቻሉ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡
የነፍስ አድን ሠራተኞች ጀልባዪቱን ያወጧት ከባህሩ 50 ሜትር ጠልቃ ከገባችበት ባህር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ከፖርቲሴሎ ወደብ ከንጋቱ 11 ሰዓት አካባቢ የተገለበጠችው ጀልባ 10 ሠራተኞች እና የእንግሊዝ፣ የአሜሪካ እና የካናዳ ዜጎችን ጨምሮ 12 ቱሪስቶችን አሳፍራ እንደነበር የጣልያን ጠረፍ ጠባቂዎች ተናግረዋል፡፡
የጣልያን የዜና ማሰራጫዎች አደጋው የደረሰው ከባድ አውሎ ነፋስ የቀላቀለው ዝናብና በውሃ ላይ የተነሳው ከፍተኛው ማዕበል ነው ብለዋል፡፡
ባዬሺያን በመባል የምትታወቀውና የብሪታኒያን ሰንደቅ ያነገበችው ጀልባ 75 ሜትር ርዝመት ያላት ሲሆን በሳምንት እስከ 195,000 ዩሮ እንደምትከራይ አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
መድረክ / ፎረም