ዋሺንግተን ዲሲ —
ከከንቲባዋ ጋር ከሃምሣ በላይ አሜሪካዊያን የንግድ ማህበረሰብ አባላት እንደሚጓዙ ተገልጿል።
ዋሺንግተን የመገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለልዑካን ቡድኑ ገለፃ ማድረጉን አስታውቋል።
እህትማማች ከተሞች የሆኑት አዲስ አበባና ዋሽንግተን ስምምነታቸውን በአዲስ መልክ ያድሳሉ ተብሏል።
ከንቲባዋ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ ዋሽንግተን ዲሲ በነበሩ ጊዜ ባደረጉላቸው ግብዣ መሠረት መሆኑን ኤምባሲው አክሎ ጠቁሟል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ