በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጊኒ የሚዲያ ተቋማት ዜና ያለመሥራት አድማ አደረጉ


ኮናክሪ፣ ጊኒ
ኮናክሪ፣ ጊኒ

በጊኒ የሚገኘው ሁንታ በፕሬስ እና በኢንተርኔት ላይ የሚያደርገውን ጫና በመቃወም፣ በምዕራብ አፍሪካዊቱ አገር የሚገኙ የግል ሚዲያ ተቋማት ዛሬ የአንድ ቀን ዜና ያለመሥራት አድማ አደረጉ።

የኢንተርኔት ሚዲያ ተቋማት በድህረ ገጻቸው የፕሬስ ነጻነት መጣሱን የሚያመላክቱ ፖስተሮችን ሲለጥፉ፣ የሬዲዮ ጣቢያዎች ደግሞ የሐዘን ሙዚቃዎችን ሲያጫውቱ ውለዋል፡፡

አድማው ትናንት ሰኞ የተጠራው፣ ወታደራዊው መንግሥት አፍሪክ ቪዥን ግሩፕ በተሰኘ ኩባንያ የሚተዳደሩ ሁለት የሬዲዮ ጣቢያዎችን እንዲዘጉ ካደረገና፣ ታዋቂ ድህረ ገጾች እና ማሕበራዊ ሚዲያዎች ተደራሽነታቸው ውስን እንዲሆን ማድረጉን ተከትሎ ነው። አገዛዙ “አገራዊ አንድነትን ያናጋሉ” ያላቸውን ተቋማት እንደሚዘጋም ዝቷል።

የቴሌ ኮምዩኒኬሽን ሚንስትሩ ኦስማኔ ዲያሎ ፤ "በአፍሪክ ቪዥን ግሩፕም ኾነ በሌሎች ኢንተርኔት ሚዲያዎች ላይ የተደረገ እገዳ የለም" ብለዋል።

ከሁለት ዓመታት በፊት ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴን አስወግዶ ሥልጣን የያዘው ወታደራዊ አገዛዝ በርካታ የተቃዋሚ መሪዎችን አስሯል። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ነገ ረቡዕ እና ሐሙስ በመዲናዋ ኮናክሪ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ አድርገዋል።

XS
SM
MD
LG